ሱራ 15 አል ሒጅር, አያት 80 – 84

  1. وَلَقَدْ كَذَّبَ أَصْحَابُ الْحِجْرِ الْمُرْسَلِينَ

    የሒጅርም ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡

    15:80
  2. وَآتَيْنَاهُمْ آيَاتِنَا فَكَانُوا عَنْهَا مُعْرِضِينَ

    ተዓምራታችንንም ሰጠናቸው፡፡ ከእርሷም ዘንጊዎች ነበሩ፡፡

    15:81
  3. وَكَانُوا يَنْحِتُونَ مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا آمِنِينَ

    ከኮረብታዎችም ቤቶችን ጸጥተኞች ኾነው ይጠርቡ ነበር፡፡

    15:82
  4. فَأَخَذَتْهُمُ الصَّيْحَةُ مُصْبِحِينَ

    ያነጉም ሲኾኑ ጩኸት ያዘቻቸው፤ (ወደሙ)፡፡

    15:83
  5. فَمَا أَغْنَىٰ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَكْسِبُونَ

    ይሠሩትም የነበሩት ነገር (ሕንጻ) ምንም አልጠቀማቸውም፡፡

    15:84

ትርጉም: Muhammad Sadiq and Muhammad al-Thani Habib