ሱራ 20 ጣሃ, አያት 49 – 52

  1. قَالَ فَمَنْ رَبُّكُمَا يَا مُوسَىٰ

    (ፈርዖንም) «ሙሳ ሆይ! ጌታችሁ ማነው?» አለ፡፡

    20:49
  2. قَالَ رَبُّنَا الَّذِي أَعْطَىٰ كُلَّ شَيْءٍ خَلْقَهُ ثُمَّ هَدَىٰ

    «ጌታችን ያ ለፍጥረቱ ነገርን ሁሉ (የሚያስፈልገውን) የሰጠ ከዚያም የመራው ነው» አለው፡፡

    20:50
  3. قَالَ فَمَا بَالُ الْقُرُونِ الْأُولَىٰ

    (ፈርዖንም) «የመጀመሪያይቱ ዘመናት ሕዝቦች ኹኔታ ምንድን ነው» አለ፡፡

    20:51
  4. قَالَ عِلْمُهَا عِنْدَ رَبِّي فِي كِتَابٍ ۖ لَا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنْسَى

    (ሙሳም) «ዕውቀትዋ እጌታዬ ዘንድ በመጽሐፍ (የተመዘገበ) ነው፡፡ ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም» አለው፡፡

    20:52

ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ