ሱራ 20 ጣሃ

  1. قَالَ لَهُمْ مُوسَىٰ وَيْلَكُمْ لَا تَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا فَيُسْحِتَكُمْ بِعَذَابٍ ۖ وَقَدْ خَابَ مَنِ افْتَرَىٰ

    ሙሳ ለእነሱ አላቸው «ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ፡፡ በቅጣት ያጠፋችኋልና፡፡ የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ፡፡»

    20:61
  2. فَتَنَازَعُوا أَمْرَهُمْ بَيْنَهُمْ وَأَسَرُّوا النَّجْوَىٰ

    (ድግምተኞቹ) በመካከላቸውም ነገራቸውን ተጨቃጨቁ፡፡ ውይይትንም ደበቁ፡፡

    20:62
  3. قَالُوا إِنْ هَٰذَانِ لَسَاحِرَانِ يُرِيدَانِ أَنْ يُخْرِجَاكُمْ مِنْ أَرْضِكُمْ بِسِحْرِهِمَا وَيَذْهَبَا بِطَرِيقَتِكُمُ الْمُثْلَىٰ

    «እነዚህ (ሁላቱ) በእርግጥ ደጋሚዎች ናቸው፡፡ ከምድራችሁ በድግምታቸው ሊያወጧችሁ በላጪቱንም መንገዳችሁን ሊያስወግዱባችሁ ይሻሉ» አሉ፡፡

    20:63
  4. فَأَجْمِعُوا كَيْدَكُمْ ثُمَّ ائْتُوا صَفًّا ۚ وَقَدْ أَفْلَحَ الْيَوْمَ مَنِ اسْتَعْلَىٰ

    «ተንኮላችሁንም አጠንክሩ፡፡ ከዚያም ተሰልፋችሁ ኑ፡፡ ዛሬ ያሸነፈም ሰው ምኞቱን አገኘ» (ተባባሉ)፡፡

    20:64
  5. قَالُوا يَا مُوسَىٰ إِمَّا أَنْ تُلْقِيَ وَإِمَّا أَنْ نَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَلْقَىٰ

    «ሙሳ ሆይ! ወይ ትጥላለህ ወይም በመጀመሪያ የምንጥል እንኾናለን» (ምረጥ) አሉ፡፡

    20:65
  6. قَالَ بَلْ أَلْقُوا ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِنْ سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ

    «አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ (እባቦች) ኾነው ወደርሱ ተመለሱ፡፡

    20:66
  7. فَأَوْجَسَ فِي نَفْسِهِ خِيفَةً مُوسَىٰ

    ሙሳም በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ፡፡

    20:67
  8. قُلْنَا لَا تَخَفْ إِنَّكَ أَنْتَ الْأَعْلَىٰ

    «አትፍራ አንተ የበላዩ አንተ ነህና» አልነው፡፡

    20:68
  9. وَأَلْقِ مَا فِي يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوا ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا كَيْدُ سَاحِرٍ ۖ وَلَا يُفْلِحُ السَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ

    «በቀኝ እጅህ ያለቸውንም (በትር) ጣል፡፡ ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፡፡ ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» (አልን)፡፡

    20:69
  10. فَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سُجَّدًا قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ هَارُونَ وَمُوسَىٰ

    ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡ «በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን» አሉ፡፡

    20:70
  11. قَالَ آمَنْتُمْ لَهُ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّهُ لَكَبِيرُكُمُ الَّذِي عَلَّمَكُمُ السِّحْرَ ۖ فَلَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُمْ مِنْ خِلَافٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِي جُذُوعِ النَّخْلِ وَلَتَعْلَمُنَّ أَيُّنَا أَشَدُّ عَذَابًا وَأَبْقَىٰ

    (ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማናጋት (ግራናቀኝን በማፈራረቅ) እቆራርጣችኋለሁ፡፡ በዘምባባም ግንዶች ለይ እሰቅላችኋለሁ፡፡ ማንኛችንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መኾኑን ታውቃላችሁ» አላቸው፡፡

    20:71
  12. قَالُوا لَنْ نُؤْثِرَكَ عَلَىٰ مَا جَاءَنَا مِنَ الْبَيِّنَاتِ وَالَّذِي فَطَرَنَا ۖ فَاقْضِ مَا أَنْتَ قَاضٍ ۖ إِنَّمَا تَقْضِي هَٰذِهِ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا

    ከመጡልን ታምራቶች ከዚያም ከፈጠረን (አምላክ) ፈጽሞ አንመርጥህም፤ አንተም የምትፈርደውን ፍረድ፤ የምትፈርደው በዚች በአነስተኛይቱ ሕይወት ብቻ ነው አሉ፡፡

    20:72
  13. إِنَّا آمَنَّا بِرَبِّنَا لِيَغْفِرَ لَنَا خَطَايَانَا وَمَا أَكْرَهْتَنَا عَلَيْهِ مِنَ السِّحْرِ ۗ وَاللَّهُ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ

    «ኃጢአቶቻችንንና ከድግምትም በእርሱ ላይ ያስገደድከንን ለእኛ ይምረን ዘንድ እኛ በጌታችን አምነናል፡፡ አላህም በጣም በላጭ ነው፤ (ቅጣቱም) በጣም የሚዘወትር ነው» አሉ፡፡

    20:73
  14. إِنَّهُ مَنْ يَأْتِ رَبَّهُ مُجْرِمًا فَإِنَّ لَهُ جَهَنَّمَ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ

    እነሆ ከሓዲ ኾኖ ወደ ጌታው የሚመጣ ሰው ለእርሱ ገሀነም አለችው፡፡ በውስጧም አይሞትም ሕያውም አይኾን፡፡

    20:74
  15. وَمَنْ يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ

    በጎ ሥራዎችን በእርግጥ የሠራ ምእመን ኾኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው፡፡

    20:75
  16. جَنَّاتُ عَدْنٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ وَذَٰلِكَ جَزَاءُ مَنْ تَزَكَّىٰ

    ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ (አሏቸው)፡፡ ይህም የተጥራራ ሰው ምንዳ ነው፡፡

    20:76
  17. وَلَقَدْ أَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَسْرِ بِعِبَادِي فَاضْرِبْ لَهُمْ طَرِيقًا فِي الْبَحْرِ يَبَسًا لَا تَخَافُ دَرَكًا وَلَا تَخْشَىٰ

    ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ በሌሊት ኺድ፡፡ ለእነሱም በባሕር ውስጥ ደረቅ መንገድን አድርግላቸው፡፡ መገኘትን አትፍራ፡፡ (ከመስጠም) አትጨነቅም፡፡» ስንል በእርግጥ ላክንበት፡፡

    20:77
  18. فَأَتْبَعَهُمْ فِرْعَوْنُ بِجُنُودِهِ فَغَشِيَهُمْ مِنَ الْيَمِّ مَا غَشِيَهُمْ

    ፈርዖንም ከሰራዊቱ ጋር ኾኖ ተከተላቸው፡፡ ከባህሩም የሚሸፍን ሸፈናቸው፡፡

    20:78
  19. وَأَضَلَّ فِرْعَوْنُ قَوْمَهُ وَمَا هَدَىٰ

    ፈርዖንም ሕዝቦቹን አሳሳታቸው፡፡ ቅኑንም መንገድ አልመራቸውም፡፡

    20:79
  20. يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ قَدْ أَنْجَيْنَاكُمْ مِنْ عَدُوِّكُمْ وَوَاعَدْنَاكُمْ جَانِبَ الطُّورِ الْأَيْمَنَ وَنَزَّلْنَا عَلَيْكُمُ الْمَنَّ وَالسَّلْوَىٰ

    የእስራኤል ልጆች ሆይ! ከጠላታችሁ በእርግጥ አዳንናችሁ፡፡ በጡርም ቀኝ ጎን ቀጠሮ አደረግንላችሁ፡፡ በእናንተም ላይ መናንና ሰልዋ (ድርጭትን) አወረድንላችሁ፡፡

    20:80

ትርጉም: Muhammad Sadiq and Muhammad al-Thani Habib