ሱራ 23 አል-ሙዕሚኑን

  1. بَلْ قَالُوا مِثْلَ مَا قَالَ الْأَوَّلُونَ

    ይልቁንም (የመካ ከሓዲዎች) የፊተኞቹ ሕዝቦች እንዳሉት ብጤ አሉ፡፡

    23:81
  2. قَالُوا أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ

    «በሞትንና ዐፈርና አጥንቶች በኾን ጊዜ እኛ ተቀስቃሾች ነን?» አሉ፡፡

    23:82
  3. لَقَدْ وُعِدْنَا نَحْنُ وَآبَاؤُنَا هَٰذَا مِنْ قَبْلُ إِنْ هَٰذَا إِلَّا أَسَاطِيرُ الْأَوَّلِينَ

    «ይህንን እኛም ከእኛ በፊትም የነበሩት አባቶቻችን በእርግጥ ተቀጥረናል፡፡ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» (አሉ)፡፡

    23:83
  4. قُلْ لِمَنِ الْأَرْضُ وَمَنْ فِيهَا إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ

    «ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)» በላቸው፡፡

    23:84
  5. سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

    «በእርግጥ የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ አትገሰጹምን?» በላቸው፡፡

    23:85
  6. قُلْ مَنْ رَبُّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ

    «የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?» በላቸው፡፡

    23:86
  7. سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ

    «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «እንግዲያ አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡

    23:87
  8. قُلْ مَنْ بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِنْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ

    «የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡

    23:88
  9. سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ

    «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡

    23:89
  10. بَلْ أَتَيْنَاهُمْ بِالْحَقِّ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ

    ይልቁንም እውነትን አመጣንላቸው፡፡ እነርሱም (በመካዳቸው) ውሸታሞች ናቸው፡፡

    23:90
  11. مَا اتَّخَذَ اللَّهُ مِنْ وَلَدٍ وَمَا كَانَ مَعَهُ مِنْ إِلَٰهٍ ۚ إِذًا لَذَهَبَ كُلُّ إِلَٰهٍ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ

    አላህ ምንም ልጅን አልያዘም (አልወለደም)፡፡ ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም፡፡ ያን ጊዜ (ሌላ አምላክ በነበረ) አምላክ ሁሉ በፈጠረው ነገር በተለየ ነበር፡፡ ከፊላቸውም በከፊሉ ለይ በላቀ ነበር፡፡ አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ፡፡

    23:91
  12. عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

    ሩቁንና ቅርቡንም ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ከፍ አለ፡፡

    23:92
  13. قُلْ رَبِّ إِمَّا تُرِيَنِّي مَا يُوعَدُونَ

    (ሙሐመድ ሆይ!) በል «ጌታዬ ሆይ! የሚያስፈራሩበትን (ቅጣት) ብታሳየኝ፡፡

    23:93
  14. رَبِّ فَلَا تَجْعَلْنِي فِي الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ

    «ጌታዬ ሆይ! በበደለኞች ሕዝቦች ውስጥ አታድርገኝ፡፡»

    23:94
  15. وَإِنَّا عَلَىٰ أَنْ نُرِيَكَ مَا نَعِدُهُمْ لَقَادِرُونَ

    እኛ የምናስፈራራቸውን ነገር ልናሳይህ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡

    23:95
  16. ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ السَّيِّئَةَ ۚ نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَصِفُونَ

    በዚያች እርስዋ መልካም በኾነችው (ጠባይ) መጥፎይቱን ነገር ገፍትር፡፡ እኛ የሚሉትን ሁሉ ዐዋቂዎች ነን፡፡

    23:96
  17. وَقُلْ رَبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ

    በልም «ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ፡፡

    23:97
  18. وَأَعُوذُ بِكَ رَبِّ أَنْ يَحْضُرُونِ

    «ባንተም ጌታዬ ሆይ! (በነገሮቼ) ወደእኔ ከመጣዳቸው እጠበቃለሁ፡፡»

    23:98
  19. حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ

    አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! (ወደ ምድረ ዓለም) መልሱኝ፡፡

    23:99
  20. لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا ۖ وَمِنْ وَرَائِهِمْ بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

    «በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» (ይህን ከማለት) ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አልለ፡፡

    23:100

ትርጉም: Muhammad Sadiq and Muhammad al-Thani Habib