ሱራ 26 አሽ ሹዐራእ, አያት 124 – 135
-
إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ هُودٌ أَلَا تَتَّقُونَ
ወንድማቸው ሁድ ለነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን?
26:124 -
إِنِّي لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ
«እኔ ለናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
26:125 -
فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
«አላህንም ፍሩ ታዘዙኝም፡፡
26:126 -
وَمَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ الْعَالَمِينَ
«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
26:127 -
أَتَبْنُونَ بِكُلِّ رِيعٍ آيَةً تَعْبَثُونَ
«የምትጫወቱ ኾናችሁ በከፍተኛ ስፍራ ሁሉ ላይ ምልክትን ትገነባላችሁን?
26:128 -
وَتَتَّخِذُونَ مَصَانِعَ لَعَلَّكُمْ تَخْلُدُونَ
«የውሃ ማጠራቀሚያዎችንና ሕንፃዎችንም ዘላለም መኖርን የምትከጅሉ ኾናችሁ ትሠራላችሁን?
26:129 -
وَإِذَا بَطَشْتُمْ بَطَشْتُمْ جَبَّارِينَ
«በቀጣችሁም ጊዜ ጨካኞች ኾናችሁ ትቀጣላችሁን?
26:130 -
فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
26:131 -
وَاتَّقُوا الَّذِي أَمَدَّكُمْ بِمَا تَعْلَمُونَ
«ያንንም በምታውቁት (ጸጋ) ያጣቀማችሁን ፍሩ፡፡
26:132 -
أَمَدَّكُمْ بِأَنْعَامٍ وَبَنِينَ
«በእንስሳዎችና በልጆች ያጣቀማችሁን፡፡
26:133 -
وَجَنَّاتٍ وَعُيُونٍ
«በአትክልቶችና በምንጮችም፡፡
26:134 -
إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ
«እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራለሁና፡፡»
26:135
ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ