ሱራ 26 አሽ ሹዐራእ, አያት 142 – 152

  1. إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ صَالِحٌ أَلَا تَتَّقُونَ

    ወንድማቸው ሷሊህ ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን ?

    26:142
  2. إِنِّي لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ

    «እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡

    26:143
  3. فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

    «አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡

    26:144
  4. وَمَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ الْعَالَمِينَ

    «በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡

    26:145
  5. أَتُتْرَكُونَ فِي مَا هَاهُنَا آمِنِينَ

    «በዚያ እዚህ ባለው (ጸጋ) ውስጥ የረካችሁ ኾናችሁ ትተዋላችሁን?

    26:146
  6. فِي جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ

    «በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ፡፡

    26:147
  7. وَزُرُوعٍ وَنَخْلٍ طَلْعُهَا هَضِيمٌ

    «በአዝመራዎችም ፍሬዋ የበሰለ በኾነች ዘንባባም፤ (ውስጥ ትተዋላችሁን)

    26:148
  8. وَتَنْحِتُونَ مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا فَارِهِينَ

    «ብልሆች ኾናችሁ ከጋራዎች ቤቶችንም ትጠርባላችሁ፡፡

    26:149
  9. فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

    «አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡

    26:150
  10. وَلَا تُطِيعُوا أَمْرَ الْمُسْرِفِينَ

    «የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ፡፡

    26:151
  11. الَّذِينَ يُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ وَلَا يُصْلِحُونَ

    «የእነዚያን በምድር ላይ የሚያጠፉትንና የማያበጁትን፡፡»

    26:152

ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ