ሱራ 26 አሽ ሹዐራእ, አያት 161 – 166
-
إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ لُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ
ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ «አትጠነቀቁምን?
26:161 -
إِنِّي لَكُمْ رَسُولٌ أَمِينٌ
«እኔ ለእናንተ ታማኝ መልክተኛ ነኝ፡፡
26:162 -
فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
«አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም፡፡
26:163 -
وَمَا أَسْأَلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِيَ إِلَّا عَلَىٰ رَبِّ الْعَالَمِينَ
«በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ በዓለማት ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም፡፡
26:164 -
أَتَأْتُونَ الذُّكْرَانَ مِنَ الْعَالَمِينَ
«ከዓለማት ሰዎች ወንዶችን ትመጣላችሁን?
26:165 -
وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمْ رَبُّكُمْ مِنْ أَزْوَاجِكُمْ ۚ بَلْ أَنْتُمْ قَوْمٌ عَادُونَ
«ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ፡፡»
26:166
ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ