ሱራ 3 ኣሊ-ኢምራን, አያት 38 – 41

  1. هُنَالِكَ دَعَا زَكَرِيَّا رَبَّهُ ۖ قَالَ رَبِّ هَبْ لِي مِنْ لَدُنْكَ ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ الدُّعَاءِ

    እዚያ ዘንድ ዘከሪያ ጌታውን ለመነ፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ አንተ ጸሎትን ሰሚነህና» አለ፡፡

    3:38
  2. فَنَادَتْهُ الْمَلَائِكَةُ وَهُوَ قَائِمٌ يُصَلِّي فِي الْمِحْرَابِ أَنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكَ بِيَحْيَىٰ مُصَدِّقًا بِكَلِمَةٍ مِنَ اللَّهِ وَسَيِّدًا وَحَصُورًا وَنَبِيًّا مِنَ الصَّالِحِينَ

    እርሱም በጸሎት ማድረሻው ክፍል ቆሞ ሲሰግድ መላእክት ጠራችው፡፡ «አላህ በየሕያ ያበስርሃል፤ ከአላህ በኾነ ቃል የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም ከደጋጎቹ ነቢይም ሲኾን » በማለት (መላእክት ጠራችው)፡፡

    3:39
  3. قَالَ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي غُلَامٌ وَقَدْ بَلَغَنِيَ الْكِبَرُ وَامْرَأَتِي عَاقِرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكَ اللَّهُ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ

    «ጌታዬ ሆይ! እኔ እርጅና በእርግጥ የደረሰብኝ ስኾን ባልተቤቴም መሐን ስትሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለ፡፡ (መልአኩም) እንደዚሁ አላህ የሚሻውን ነገር ይሠራል» አለው፡፡

    3:40
  4. قَالَ رَبِّ اجْعَلْ لِي آيَةً ۖ قَالَ آيَتُكَ أَلَّا تُكَلِّمَ النَّاسَ ثَلَاثَةَ أَيَّامٍ إِلَّا رَمْزًا ۗ وَاذْكُرْ رَبَّكَ كَثِيرًا وَسَبِّحْ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ

    «ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ምልክትን አድርግልኝ» አለ፡፡ «ምልክትህ ሦስት ቀን በጥቅሻ ቢኾን እንጅ ሰዎችን አለማናገርህ ነው፡፡ ጌታህንም በብዙ አውሳ፡፡ በማታና በጧትም አወድሰው» አለው፡፡

    3:41

ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ