ሱራ 90 አል በለድ, አያት 13 – 18

  1. فَكُّ رَقَبَةٍ

    (እርሱ) ጫንቃን መልቀቅ ነው፡፡

    90:13
  2. أَوْ إِطْعَامٌ فِي يَوْمٍ ذِي مَسْغَبَةٍ

    ወይም የረኃብ ባለቤት በኾነ ቀን ማብላት፡፡

    90:14
  3. يَتِيمًا ذَا مَقْرَبَةٍ

    የዝምድና ባለቤት የኾነን የቲም፤

    90:15
  4. أَوْ مِسْكِينًا ذَا مَتْرَبَةٍ

    ወይም የዐፈር ባለቤት የኾነን ድኻ (ማብላት ነው)፡፡

    90:16
  5. ثُمَّ كَانَ مِنَ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ وَتَوَاصَوْا بِالْمَرْحَمَةِ

    ከዚያም ከነዚያ ከአመኑትና በመታገስ አደራ ከተባባሉት፣ በማዘንም አደራ ከተባባሉት ሰዎች ጋር መሆን ነው፡፡

    90:17
  6. أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْمَيْمَنَةِ

    እነዚያ (ይህንን የፈጸሙ) የቀኝ ጓዶች ናቸው፡፡

    90:18

ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ