ሙሳፍ, ገጽ 301
-
فَلَمَّا جَاوَزَا قَالَ لِفَتَاهُ آتِنَا غَدَاءَنَا لَقَدْ لَقِينَا مِنْ سَفَرِنَا هَٰذَا نَصَبًا
ባለፉም ጊዜ ለወጣቱ «ምሳችንን ስጠን፡፡ ከዚህ ጉዟችን በእርግጥ ድካምን አግኝተናልና» አለ፡፡
18:62 -
قَالَ أَرَأَيْتَ إِذْ أَوَيْنَا إِلَى الصَّخْرَةِ فَإِنِّي نَسِيتُ الْحُوتَ وَمَا أَنْسَانِيهُ إِلَّا الشَّيْطَانُ أَنْ أَذْكُرَهُ ۚ وَاتَّخَذَ سَبِيلَهُ فِي الْبَحْرِ عَجَبًا
«አየህን ወደ ቋጥኝዋ በተጠጋን ጊዜ እኔ ዐሣውን ረሳሁ፡፡ ማስታወሱንም ሰይጣን እንጂ ሌላ አላስረሳኝም፡፡ በባሕሩም ውስጥ መንገዱን አስደናቂ (መንገድ) አድርጎ ያዘ» አለ፡፡
18:63 -
قَالَ ذَٰلِكَ مَا كُنَّا نَبْغِ ۚ فَارْتَدَّا عَلَىٰ آثَارِهِمَا قَصَصًا
(ሙሳም) ይህ እንፈልገው የነበርነው ነው አለው፡፡ በፈለጎቻቸውም ላይ እየተከተሉ ተመለሱ፡፡
18:64 -
فَوَجَدَا عَبْدًا مِنْ عِبَادِنَا آتَيْنَاهُ رَحْمَةً مِنْ عِنْدِنَا وَعَلَّمْنَاهُ مِنْ لَدُنَّا عِلْمًا
ከባሮቻችንም ከእኛ ዘንድ ችሮታን የሰጠነውን ከእኛም ዘንድ ዕውቀትን ያስተማርነውን አንድን ባሪያ (ኸደርን) አገኙ፡፡
18:65 -
قَالَ لَهُ مُوسَىٰ هَلْ أَتَّبِعُكَ عَلَىٰ أَنْ تُعَلِّمَنِ مِمَّا عُلِّمْتَ رُشْدًا
ሙሳ ለእርሱ «ከተማርከው ነገር ቀጥተኛን (ዕውቀት) ታስተምረኝ ዘንድ ልከተልህን?» አለው፡፡
18:66 -
قَالَ إِنَّكَ لَنْ تَسْتَطِيعَ مَعِيَ صَبْرًا
(ባሪያውም) አለ «አንተ ከእኔ ጋር መታገስን በጭራሽ አትችልም፡፡
18:67 -
وَكَيْفَ تَصْبِرُ عَلَىٰ مَا لَمْ تُحِطْ بِهِ خُبْرًا
«በዕውቀትም በእርሱ ባላዳረስከው ነገር ላይ እንዴት ትታገሳለህ?»
18:68 -
قَالَ سَتَجِدُنِي إِنْ شَاءَ اللَّهُ صَابِرًا وَلَا أَعْصِي لَكَ أَمْرًا
(ሙሳ) «አላህ የሻ እንደ ኾነ ታጋሽና ላንተ ትዕዛዝን የማልጥስ ኾኜ ታገኘኛለህ» አለው፡፡
18:69 -
قَالَ فَإِنِ اتَّبَعْتَنِي فَلَا تَسْأَلْنِي عَنْ شَيْءٍ حَتَّىٰ أُحْدِثَ لَكَ مِنْهُ ذِكْرًا
«ብትከተለኝም ለአንተ ከእርሱ ማውሳትን እስከምጀምርልህ ድረስ ከምንም ነገር አትጠይቀኝ» አለው፡፡
18:70 -
فَانْطَلَقَا حَتَّىٰ إِذَا رَكِبَا فِي السَّفِينَةِ خَرَقَهَا ۖ قَالَ أَخَرَقْتَهَا لِتُغْرِقَ أَهْلَهَا لَقَدْ جِئْتَ شَيْئًا إِمْرًا
ኼዱም፡፡ በመርከቢቱም በተሳፈሩ ጊዜ ቀደዳት፡፡ «ባለ ቤቶቿን ልታሰጥም ቀደድካትን ትልቅ ነገርን በእርግጥ ሠራህ» አለው፡፡
18:71 -
قَالَ أَلَمْ أَقُلْ إِنَّكَ لَنْ تَسْتَطِيعَ مَعِيَ صَبْرًا
«አንተ ከኔ ጋር ትእግሥትን ፈጽሞ አትችልም አላልኩምን?» አለ፡፡
18:72 -
قَالَ لَا تُؤَاخِذْنِي بِمَا نَسِيتُ وَلَا تُرْهِقْنِي مِنْ أَمْرِي عُسْرًا
«በረሳሁት ነገር አትያዘኝ፡፡ ከነገሬም ችግርን አታሸክመኝ» አለው፡፡
18:73 -
فَانْطَلَقَا حَتَّىٰ إِذَا لَقِيَا غُلَامًا فَقَتَلَهُ قَالَ أَقَتَلْتَ نَفْسًا زَكِيَّةً بِغَيْرِ نَفْسٍ لَقَدْ جِئْتَ شَيْئًا نُكْرًا
(ወርደው) ተጓዙም፡፡ ወጣትንም ልጅ ባገኙና በገደለው ጊዜ ፤«ያለ ነፍስ (መግደል) ንጹሕን ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎን ነገር ሠራህ» አለው፡፡
18:74
ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ