ሙሳፍ, ገጽ 321

  1. قَالَ كَذَٰلِكَ أَتَتْكَ آيَاتُنَا فَنَسِيتَهَا ۖ وَكَذَٰلِكَ الْيَوْمَ تُنْسَىٰ

    (ነገሩ) እንደዚሁ ነው፡፡ «ታምራታችን መጣችልህ፡፡ ተውካትም፡፡ እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ» ይለዋል፡፡

    20:126
  2. وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي مَنْ أَسْرَفَ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِآيَاتِ رَبِّهِ ۚ وَلَعَذَابُ الْآخِرَةِ أَشَدُّ وَأَبْقَىٰ

    እንደዚሁም ያጋራንና በጌታው አንቀጾች ያላመነን ሰው እንቀጣዋለን፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ብርቱ ሁልጊዜ ዘውታሪም ነው፡፡

    20:127
  3. أَفَلَمْ يَهْدِ لَهُمْ كَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُمْ مِنَ الْقُرُونِ يَمْشُونَ فِي مَسَاكِنِهِمْ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِأُولِي النُّهَىٰ

    (ቁረይሾች) ከእነሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ያጠፋን መኾናችን በመኖሪያዎቻቸው የሚኼዱ ኾነው ሳሉ ለእነርሱ አልተገለጸላቸውምን؟ በዚህ ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መልክቶች አሉበት፡፡

    20:128
  4. وَلَوْلَا كَلِمَةٌ سَبَقَتْ مِنْ رَبِّكَ لَكَانَ لِزَامًا وَأَجَلٌ مُسَمًّى

    ከጌታህ ያለፈች ቃልና የተወሰነ ጊዜ ባልነበረ ኖሮ (ቅጣቱ አሁኑኑ) የሚይዛቸው ይኾን ነበር፡፡

    20:129
  5. فَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا ۖ وَمِنْ آنَاءِ اللَّيْلِ فَسَبِّحْ وَأَطْرَافَ النَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرْضَىٰ

    በሚሉትም ላይ ታገስ፡፡ ጌታህንም ፀሐይ ከመውጣትዋ በፊት ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ኾነህ አጥራው፤ (ስገድ)፡፡ ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው፡፡ (በሚሰጥህ ምንዳ) ልትወድ ይከጀላልና፡፡

    20:130
  6. وَلَا تَمُدَّنَّ عَيْنَيْكَ إِلَىٰ مَا مَتَّعْنَا بِهِ أَزْوَاجًا مِنْهُمْ زَهْرَةَ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا لِنَفْتِنَهُمْ فِيهِ ۚ وَرِزْقُ رَبِّكَ خَيْرٌ وَأَبْقَىٰ

    ዓይኖችህንም ከእነርሱ (ከሰዎቹ) ክፍሎችን በእርሱ ልንፈትናቸው ወደ አጣቀምንበት፤ ወደ ቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች አትዘርጋ፡፡ የጌታህ ሲሳይም በጣም በላጭ ዘውታሪም ነው፡፡

    20:131
  7. وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ

    ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤ (ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ ሲሳይን እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡

    20:132
  8. وَقَالُوا لَوْلَا يَأْتِينَا بِآيَةٍ مِنْ رَبِّهِ ۚ أَوَلَمْ تَأْتِهِمْ بَيِّنَةُ مَا فِي الصُّحُفِ الْأُولَىٰ

    «ከጌታውም በኾነ ተዓምር አይመጣንምን?» አሉ በመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች ውስጥ ያለችው ማስረጃ አልመጣቻቸውምን?

    20:133
  9. وَلَوْ أَنَّا أَهْلَكْنَاهُمْ بِعَذَابٍ مِنْ قَبْلِهِ لَقَالُوا رَبَّنَا لَوْلَا أَرْسَلْتَ إِلَيْنَا رَسُولًا فَنَتَّبِعَ آيَاتِكَ مِنْ قَبْلِ أَنْ نَذِلَّ وَنَخْزَىٰ

    እኛም ከእርሱ (ከሙሐመድ መላክ) በፊት በቅጣት ባጠፋናቸው ኖሮ «ጌታችን ሆይ! ከመዋረዳችንና ከማፈራችን በፊት አንቀጾችህን እንከተል ዘንድ ወደኛ መልከተኛን አትልክም ነበርን?» ባሉ ነበር፡፡

    20:134
  10. قُلْ كُلٌّ مُتَرَبِّصٌ فَتَرَبَّصُوا ۖ فَسَتَعْلَمُونَ مَنْ أَصْحَابُ الصِّرَاطِ السَّوِيِّ وَمَنِ اهْتَدَىٰ

    «ሁሉም ተጠባባቂ ነው፡፡ ተጠባበቁም፡፡ የቀጥታውም መንገድ ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ እነማንም እንደ ተመሩ ወደ ፊት ታውቃላችሁ» በላቸው፡፡

    20:135

ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ