ሙሳፍ, ገጽ 369

  1. لَعَلَّنَا نَتَّبِعُ السَّحَرَةَ إِنْ كَانُوا هُمُ الْغَالِبِينَ

    «ድግምተኞቹን እነሱ አሸናፊዎች ቢኾኑ እንከተል ዘንድ» (ተባለ)፡፡

    26:40
  2. فَلَمَّا جَاءَ السَّحَرَةُ قَالُوا لِفِرْعَوْنَ أَئِنَّ لَنَا لَأَجْرًا إِنْ كُنَّا نَحْنُ الْغَالِبِينَ

    «ድግምተኞቹም በመጡ ጊዜ ለፈርዖን እኛ አሸናፊዎች ብንሆን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን?» አሉት፡፡

    26:41
  3. قَالَ نَعَمْ وَإِنَّكُمْ إِذًا لَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

    «አዎን፤ እናንተም ያን ጊዜ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡

    26:42
  4. قَالَ لَهُمْ مُوسَىٰ أَلْقُوا مَا أَنْتُمْ مُلْقُونَ

    ሙሳ «ለእነርሱ እናንተ የምትጥሉትን ጣሉ» አላቸው፡፡

    26:43
  5. فَأَلْقَوْا حِبَالَهُمْ وَعِصِيَّهُمْ وَقَالُوا بِعِزَّةِ فِرْعَوْنَ إِنَّا لَنَحْنُ الْغَالِبُونَ

    ገመዶቻቸውንና በትሮቻቸውንም ጣሉ፡፡ «በፈርዖንም ክብር ይኹንብን፡፡ እኛ በእርግጥ አሸናፊዎቹ እኛ ነን» አሉ፡፡

    26:44
  6. فَأَلْقَىٰ مُوسَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ

    ሙሳም በትሩን ጣለ፡፡ ወዲያውም እርሷ የሚያስመስሉትን ሁሉ ትውጣለች፡፡

    26:45
  7. فَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سَاجِدِينَ

    ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡

    26:46
  8. قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ الْعَالَمِينَ

    (እነሱም) አሉ «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡

    26:47
  9. رَبِّ مُوسَىٰ وَهَارُونَ

    «በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡»

    26:48
  10. قَالَ آمَنْتُمْ لَهُ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّهُ لَكَبِيرُكُمُ الَّذِي عَلَّمَكُمُ السِّحْرَ فَلَسَوْفَ تَعْلَمُونَ ۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُمْ مِنْ خِلَافٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ

    (ፈርዖንም) «ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው፡፡ ወደፊትም (የሚያገኛችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (ቀኝና ግራን) በማናጋት እቆረርጣለሁ፡፡ ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁም» አለ፡፡

    26:49
  11. قَالُوا لَا ضَيْرَ ۖ إِنَّا إِلَىٰ رَبِّنَا مُنْقَلِبُونَ

    (እነርሱም) አሉ «ጉዳት የለብንም፡፡ እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡

    26:50
  12. إِنَّا نَطْمَعُ أَنْ يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَايَانَا أَنْ كُنَّا أَوَّلَ الْمُؤْمِنِينَ

    «እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡»

    26:51
  13. وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنْ أَسْرِ بِعِبَادِي إِنَّكُمْ مُتَّبَعُونَ

    ወደ ሙሳም «ባሮቼን ይዘህ ሌሊት ኺድ፡፡ እናንተ የሚከተሉዋችሁ ናችሁና» ስንል ላክን፡፡

    26:52
  14. فَأَرْسَلَ فِرْعَوْنُ فِي الْمَدَائِنِ حَاشِرِينَ

    ፈርዖንም በየከተሞቹ ሰብሳቢዎችን (እንዲህ ሲል) ላከ፡፡

    26:53
  15. إِنَّ هَٰؤُلَاءِ لَشِرْذِمَةٌ قَلِيلُونَ

    «እነዚህ ጥቂቶች ጭፈሮች ናቸው፡፡

    26:54
  16. وَإِنَّهُمْ لَنَا لَغَائِظُونَ

    «እነርሱም ለእኛ አስቆጪዎች ናቸው፡፡

    26:55
  17. وَإِنَّا لَجَمِيعٌ حَاذِرُونَ

    «እኛም ብዙዎች ጥንቁቆች ነን፤» (አለ)፡፡

    26:56
  18. فَأَخْرَجْنَاهُمْ مِنْ جَنَّاتٍ وَعُيُونٍ

    አወጣናቸውም፡፡ ከአትክልቶችና ከምንጮች፡፡

    26:57
  19. وَكُنُوزٍ وَمَقَامٍ كَرِيمٍ

    ከድልቦችም ከመልካም መቀመጫዎችም፡፡

    26:58
  20. كَذَٰلِكَ وَأَوْرَثْنَاهَا بَنِي إِسْرَائِيلَ

    እንደዚሁ ለእስራኤል ልጆች አወረስናትም፡፡

    26:59
  21. فَأَتْبَعُوهُمْ مُشْرِقِينَ

    ፀሐይዋ ስትወጣም ተከተሉዋቸው፡፡

    26:60

ትርጉም: Muhammad Sadiq and Muhammad al-Thani Habib