ሙሳፍ, ገጽ 465
-
أَوْ تَقُولَ لَوْ أَنَّ اللَّهَ هَدَانِي لَكُنْتُ مِنَ الْمُتَّقِينَ
ወይም «አላህ በመራኝ ኖሮ ከሚጠነቀቁት እኾን ነበር» ማለቷን (ለመፍራት)፡፡
39:57 -
أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى الْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِي كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ الْمُحْسِنِينَ
ወይም ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ (ወደ ምድረ ዓለም) አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን (ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ)፡፡
39:58 -
بَلَىٰ قَدْ جَاءَتْكَ آيَاتِي فَكَذَّبْتَ بِهَا وَاسْتَكْبَرْتَ وَكُنْتَ مِنَ الْكَافِرِينَ
የለም (ተመርተሃል)፡፡ አንቀጾቼ በእርግጥ መጥተውልሃል፡፡ በእነርሱም አስተባብለሃል፡፡ ኮርተሃልም፡፡ ከከሓዲዎቹም ኾነሃል፤ (ይባላል)፡፡
39:59 -
وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ تَرَى الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَى اللَّهِ وُجُوهُهُمْ مُسْوَدَّةٌ ۚ أَلَيْسَ فِي جَهَنَّمَ مَثْوًى لِلْمُتَكَبِّرِينَ
በትንሣኤ ቀንም እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን ፊቶቻቸው የጠቆሩ ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?
39:60 -
وَيُنَجِّي اللَّهُ الَّذِينَ اتَّقَوْا بِمَفَازَتِهِمْ لَا يَمَسُّهُمُ السُّوءُ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
እነዚያንም የተጠነቀቁትን በማግኛቸው ስፍራ ኾነው አላህ ያድናቸዋል፡፡ ክፉ ነገር አይነካቸውም፡፡ እነርሱም አያዝኑም፡፡
39:61 -
اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡
39:62 -
لَهُ مَقَالِيدُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَالَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ أُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ
የሰማያትና የምድር (ድልብ) መክፈቻዎች የእርሱ ብቻ ናቸው፡፡ እነዚያም በአላህ አንቀጾች የካዱት እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡
39:63 -
قُلْ أَفَغَيْرَ اللَّهِ تَأْمُرُونِّي أَعْبُدُ أَيُّهَا الْجَاهِلُونَ
«እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድግገዛ ታዙኛላችሁን?» በላቸው፡፡
39:64 -
وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِنْ قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ
ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡
39:65 -
بَلِ اللَّهَ فَاعْبُدْ وَكُنْ مِنَ الشَّاكِرِينَ
ይልቅ አላህን ብቻ ተገዛም፡፡ ከአመስጋኞቹም ኹን፡፡
39:66 -
وَمَا قَدَرُوا اللَّهَ حَقَّ قَدْرِهِ وَالْأَرْضُ جَمِيعًا قَبْضَتُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَالسَّمَاوَاتُ مَطْوِيَّاتٌ بِيَمِينِهِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
አላህንም በትንሣኤ ቀን ምድር በመላ ጭብጡ ስትኾን፤ ሰማያትም በቀኝ እጁ የሚጠቀለሉ ሲኾኑ (ከርሱ ጋር ሌላን በማጋራታቸው) ተገቢ ክብሩን አላከበሩትም፡፡ ከሚያጋሩት ጠራ፤ ላቀም፡፡
39:67
ትርጉም: Muhammad Sadiq and Muhammad al-Thani Habib