ሱራ 4 አን-ኒሳዕ, አያት 25

  1. وَمَنْ لَمْ يَسْتَطِعْ مِنْكُمْ طَوْلًا أَنْ يَنْكِحَ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ فَمِنْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ مِنْ فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ ۚ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِإِيمَانِكُمْ ۚ بَعْضُكُمْ مِنْ بَعْضٍ ۚ فَانْكِحُوهُنَّ بِإِذْنِ أَهْلِهِنَّ وَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ بِالْمَعْرُوفِ مُحْصَنَاتٍ غَيْرَ مُسَافِحَاتٍ وَلَا مُتَّخِذَاتِ أَخْدَانٍ ۚ فَإِذَا أُحْصِنَّ فَإِنْ أَتَيْنَ بِفَاحِشَةٍ فَعَلَيْهِنَّ نِصْفُ مَا عَلَى الْمُحْصَنَاتِ مِنَ الْعَذَابِ ۚ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَشِيَ الْعَنَتَ مِنْكُمْ ۚ وَأَنْ تَصْبِرُوا خَيْرٌ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ

    ከናንተም ውስጥ ጥብቆች ምእምናት የኾኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ወጣቶቻችሁ (ባሪያን ያግባ)፡፡ አላህም እምነታችሁን ዐዋቂ ነው፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ (የተራባ) ነው፡፡ (ባሮችን) በጌቶቻቸውም ፈቃድ አግቡዋቸው፡፡ መህሮቻቸውንም በመልካም መንገድ ስጧቸው፡፡ ጥብቆች ኾነው ዝሙተኞች ያልኾኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኾኑ (አግቧቸው)፡፡ በማግባት በተጠበቁም ጊዜ መጥፎን ሥራ ቢሠሩ በእነርሱ ላይ ከቅጣት በነጻዎቹ ላይ ያለው ግማሽ አለባቸው፡፡ ይኸ (ባሪያን ማግባት) ከናንተ ዝሙትን ለፈራ ሰው ነው፡፡ መታገሳችሁ ለናንተ በላጭ ነው። አላህም መሓሪ አዛኝ ነው።

    4:25

ትርጉም: Muhammad Sadiq and Muhammad al-Thani Habib