ሙሳፍ, ገጽ 349

  1. أَلَمْ تَكُنْ آيَاتِي تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَكُنْتُمْ بِهَا تُكَذِّبُونَ

    «አንቀጾቼ በእናንተ ላይ የሚነበቡላችሁና በእነርሱ የምታስተባብሉ አልነበራችሁምን?» (ይባላሉ)፡፡

    23:105
  2. قَالُوا رَبَّنَا غَلَبَتْ عَلَيْنَا شِقْوَتُنَا وَكُنَّا قَوْمًا ضَالِّينَ

    ይላሉ «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ መናጢነታችን አሸነፈችን፡፡ ጠማማዎችም ሕዝቦች ነበርን፡፡

    23:106
  3. رَبَّنَا أَخْرِجْنَا مِنْهَا فَإِنْ عُدْنَا فَإِنَّا ظَالِمُونَ

    «ጌታችን ሆይ! ከእርሷ አውጣን፡፡ (ወደ ክህደት) ብንመለስ እኛ በደዮች ነን፡፡»

    23:107
  4. قَالَ اخْسَئُوا فِيهَا وَلَا تُكَلِّمُونِ

    (አላህም) «ወራዶች ኾናችሁ በውስጥዋ እርጉ፡፡ አታናግሩኝም» ይላቸዋል፡፡

    23:108
  5. إِنَّهُ كَانَ فَرِيقٌ مِنْ عِبَادِي يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا وَأَنْتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ

    እነሆ ከባሮቼ «ጌታችን ሆይ! አምነናልና ማረን እዘንልንም አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» የሚሉ ክፍሎች ነበሩ፡፡

    23:109
  6. فَاتَّخَذْتُمُوهُمْ سِخْرِيًّا حَتَّىٰ أَنْسَوْكُمْ ذِكْرِي وَكُنْتُمْ مِنْهُمْ تَضْحَكُونَ

    እኔንም ማውሳትን እስካስረሷችሁ ድረስም ማላገጫ አድርጋችሁ ያዛችኋቸው፡፡ በእነርሱም የምትስቁ ነበራችሁ፡፡

    23:110
  7. إِنِّي جَزَيْتُهُمُ الْيَوْمَ بِمَا صَبَرُوا أَنَّهُمْ هُمُ الْفَائِزُونَ

    እኔ ዛሬ በትዕግስታቸው ምክንያት እነሱ ፍላጎታቸውን የሚያገኙት እነርሱ ብቻ በመኾን መነዳኋቸው፤ (ይላቸዋል)፡፡

    23:111
  8. قَالَ كَمْ لَبِثْتُمْ فِي الْأَرْضِ عَدَدَ سِنِينَ

    «በምድር ውስጥ ከዓመታት ቁጥር ስንትን ቆያችሁ؟» ይላቸዋል፡፡

    23:112
  9. قَالُوا لَبِثْنَا يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ فَاسْأَلِ الْعَادِّينَ

    «አንድ ቀንን ወይም ከፊል ቀንን ቆየን፡፡ ቆጣሪዎቹንም ጠይቅ» ይላሉ፡፡

    23:113
  10. قَالَ إِنْ لَبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا ۖ لَوْ أَنَّكُمْ كُنْتُمْ تَعْلَمُونَ

    «እናንተ (የቆያችሁትን መጠን) የምታውቁ ብትኾኑ ኖሮ (በእሳት ውስጥ በምትቆዩት አንፃር) ጥቂትን ጊዜ እንጂ አልቆያችሁም» ይላቸዋል፡፡

    23:114
  11. أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ

    «የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን አሰባችሁን؟» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን?)

    23:115
  12. فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۖ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ

    የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡

    23:116
  13. وَمَنْ يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِنْدَ رَبِّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ

    ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለው (መሆኑ እየታወቀ) የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡

    23:117
  14. وَقُلْ رَبِّ اغْفِرْ وَارْحَمْ وَأَنْتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ

    በልም «ጌታዬ ሆይ ማር፤ እዘንም፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»

    23:118

ትርጉም: ሙሐመድ ሳዲቅ እና ሙሐመድ አስ-ሳኒ ሀቢብ